በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ማህበረሰቡን ያሳተፈ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለፀ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለረጅም ጊዜ ለነዋሪዎች ችግር ሆኖ የቆየውን የፍሳሽና የውሃ ቱቦ ብልሽት፣ እና የጋራ መፀዳጃ ቤት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተገንብቶ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ የልማት ስራ የመንግስትንና የህዝቡን አቅም በማቀናጀት ረገድ እንደ ትልቅ ስኬት ተወስዷል። በወረዳ 10 አንዳንደ አካባቢዎች የቆዩ የፍሳሽ ቱቦዎች በመሰባበራቸውና በመደፈናቸው ምክንያት፣ ነዋሪዎች ለጤና ጠንቅና ሲጋለጡ ቆይተዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ወረዳው ከነዋሪዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። የዘንድሮውን የልማት ስራ ለየት የሚያደርገው የማህበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ ነው። በጉልበትና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣የጥገና ስራው በሚከናወንበት ወቅት ተለዋጭ መንገዶችን በመጠቆምና ስራውን በመከታተል፣ የልማት ስራው ባለቤት በመሆን ከፍተኛ አርአያነት ያለው ስራ አሳይቷል

 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ማህበረሰቡን ያሳተፈ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለፀ





Comments

Popular posts from this blog

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሾን ቢሮ ከኢትዮጽያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለዉን የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ::

የመረጃ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የአገልጋይነት መንፈስን በማጠናከርና የመንግሥትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ለኅብረተሰቡ በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ።