የመረጃ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የአገልጋይነት መንፈስን በማጠናከርና የመንግሥትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ለኅብረተሰቡ በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ።
የመረጃ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የአገልጋይነት መንፈስን በማጠናከርና የመንግሥትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ለኅብረተሰቡ በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨
ጥር 25/2018
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ 6 ወር የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ትክክለኛ እና ፈጣን መረጃዎችን ማድረስ መቻሉን አስታውቋል።
የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ኑርሀሰን ጀማል እንደገለፁት የአስተዳደሩን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር በርካታ ተግባራት መከናወኑን አስታዉቀዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ አጀንዳዎች የህትመት ስራዎች አዘጋጅቶ ማሰራጨት ፣ የእቅድ እና ጥቆማ ዜናዎች ማሰራጨት የፎቶ ማንሳትና የቪድዮ ቀረፃ ስራዎች ፣ የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት መስጠት መቻሉንም ተናግረዋል።
የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የሚያሳዩ የተለያዩ አጫጭር ፕሮግራሞች ፣ ኤዲቲንግ ስራዎች ፣ ፓናሎች ፣ ሁነቶች ፣ እንጠያየቅ መድረኮች ፣ የፎቶ አውደ ርዕይ እና ሌሎች ተግባራትን በማከናወን ለህብረተሰቡ መረጃ ማድረስ መቻሉንም አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ሁሉንም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ወቅታዊና ጥራት ያላቸው ሀገር አቀፍ ብሎም ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ዙሪያ ለህብረተሰቡ መረጃዎችን ማድረስ እንደተቻለ አቶ ኑርሀሰን ገልፀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ህብረተሰቡ በቀላሉ መረጃዎችን እንዲያገኝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መንግስት የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን የማስተዋወቅ እንዲሁም በሌማት ትሩፋት ስራዎችን ተጠቃሚ ፤ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶችን ለህብረተሰቡ አገልግሎት ክፍት መሆናቸው ላይ ፣ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለህብረተሰቡ መረጃ እንዲደርስ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ስራ መሰራቱን አንስተዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች እንዲደርሱ እና ለህብረተሰቡ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች ዘወትር እሮብና አርብ ምልከታ እየተደረገ መሆኑንና የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎች መስራት እንደተቻለም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም መረጃዎችን በስፋትና በጥራት ተደራሽ በማድረግ በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብ በመፍጠር በሁለንተናዊ የልማት ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ተግባራት በመስራት ለህብረተሰቡ መረጃ ማድረስ እንደተቻለም አስታውቀዋል።

Comments
Post a Comment