Posts

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ማህበረሰቡን ያሳተፈ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለፀ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለረጅም ጊዜ ለነዋሪዎች ችግር ሆኖ የቆየውን የፍሳሽና የውሃ ቱቦ ብልሽት፣ እና የጋራ መፀዳጃ ቤት ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተገንብቶ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ የልማት ስራ የመንግስትንና የህዝቡን አቅም በማቀናጀት ረገድ እንደ ትልቅ ስኬት ተወስዷል። በወረዳ 10 አንዳንደ አካባቢዎች የቆዩ የፍሳሽ ቱቦዎች በመሰባበራቸውና በመደፈናቸው ምክንያት፣ ነዋሪዎች ለጤና ጠንቅና ሲጋለጡ ቆይተዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ወረዳው ከነዋሪዎች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። የዘንድሮውን የልማት ስራ ለየት የሚያደርገው የማህበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ ነው። በጉልበትና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣የጥገና ስራው በሚከናወንበት ወቅት ተለዋጭ መንገዶችን በመጠቆምና ስራውን በመከታተል፣ የልማት ስራው ባለቤት በመሆን ከፍተኛ አርአያነት ያለው ስራ አሳይቷል

Image
  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ማህበረሰቡን ያሳተፈ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለፀ

የመረጃ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የአገልጋይነት መንፈስን በማጠናከርና የመንግሥትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ለኅብረተሰቡ በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ።

Image
 የመረጃ ሥርዓቱን በማዘመን፣ የአገልጋይነት መንፈስን በማጠናከርና የመንግሥትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ለኅብረተሰቡ በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨፨፨፨ ጥር 25/2018 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ 6 ወር የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ትክክለኛ እና ፈጣን መረጃዎችን ማድረስ መቻሉን አስታውቋል። የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ኑርሀሰን ጀማል እንደገለፁት የአስተዳደሩን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር በርካታ ተግባራት መከናወኑን አስታዉቀዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ አጀንዳዎች የህትመት ስራዎች አዘጋጅቶ ማሰራጨት ፣ የእቅድ እና ጥቆማ ዜናዎች ማሰራጨት የፎቶ ማንሳትና የቪድዮ ቀረፃ ስራዎች ፣ የዲጂታል ሚዲያ አገልግሎት መስጠት መቻሉንም ተናግረዋል። የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች የሚያሳዩ የተለያዩ አጫጭር ፕሮግራሞች ፣ ኤዲቲንግ ስራዎች ፣ ፓናሎች ፣ ሁነቶች ፣ እንጠያየቅ መድረኮች ፣ የፎቶ አውደ ርዕይ እና ሌሎች ተግባራትን በማከናወን ለህብረተሰቡ መረጃ ማድረስ መቻሉንም አብራርተዋል። በሌላ በኩል ሁሉንም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ወቅታዊና ጥራት ያላቸው ሀገር አቀፍ ብሎም ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ዙሪያ  ለህብረተሰቡ መረጃዎችን ማድረስ እንደተቻለ አቶ ኑርሀሰን ገልፀዋል። ኃላፊው አያይዘውም ህብረተሰቡ በቀላሉ መረጃዎችን እንዲያገኝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መንግስት የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን የማስተዋወቅ እንዲሁም በሌማት ትሩፋት ስራዎችን ተጠቃሚ ፤ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶ...

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሾን ቢሮ ከኢትዮጽያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለዉን የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ::

 በዛሬዉ ዕለት የሁለቱ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት  በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የስምምነት ፊርማ አከናዉነዋል። በስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚዓብሔር እንደተናገሩት ሁለቱ ተቋማት አብረዉ በጋራ በሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ላይ ተገናኝተዉ  መወያየታቸዉን እና የዛሬዉ የስምምነት ፊርማም ይህንኑ መሠረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዉ በከተማዋ ዘርፈ ብዙ የልማት ሰራዎች  እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ነዉ ብለዋል ። ሃላፊው አክለዉም ስራዎቻችን በብዝሀ ቋንቋን ማዕከል በማድረግ ፤ የከተማችንን ገፅታ  በመገንባት በመንግስት እና በህዝብ መካከል እያደገ የመጣዉን ጠንካራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር  ያለመ ነዉ በማለት አብሮ ለመስራት የተፈጠረዉን እድል በቢሮዉ ስም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።  የኢትዮጽያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ በበኩላቸዉ ከተማችን አዲስ አበባ የኢትዮጽያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በምታደርገዉ ጉዞ  የአዲስ አበብ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ  ከኢቢሲ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት በተግባር ትብብሩን ማሳየቱ እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዉ ይህን ስኬታማ ጉዞ ዳር ለማድረስ  የነበረዉን ግንኙነታችንን በማጠናከር ባሉት በሚዲያ አማራጮቻችን ለመስራት  ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል ። ሃላፊው አክለውም ይህ የስምምነት ፊርማ ዘላቂ ትስስርን የሚፈጥር እና  የከተማዋ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ጥራት ባለዉ መልኩ ለመስራት የሚያስችለን የጋራ አጀንዳችን ነዉም  ብለዋል።

blog

 ውብ ፅዱ አዲስ አበባ